ትምህርት ቤቱ ምንድነው ?

ዙሪክ ራስ አገዝ ትምህርት ቤት (ASZ)

ትምህርት ቤቱ ዘረኝነትን የፍትህ መጉዋደልን ለመታደግ የተቁዋቁዋመ ፕሮጀክት ሲሆን ትምህርት ቤቱ የተለያዩ ሰዎች የሚገናኙበት የሚተዋወቁበትና ሃሳባቸውን የሚለዋወጡበት መገናኛ ማእከል ነው ።

ትምህርት ቤቱ በራስ ኣገዝ የተደራጀ ሲሆን ከመንግስታዊ ኣካላት ምንም ግንኙነት የለውም።ትምህርት ቤቱ በመንግስት የማይተዳደር ነው።

ትምህርት ቤቱ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን የሚያገኘው ከግለሰቦች ከማህበራትና ከድርጅቶች በኣይነት ወይም በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ትምህርት ቤቱ ኣላማውን ከሚያከብሩ ማናቸውም ተቁዋማት ድጋፍን ይቀበላል።

በትምህርት ቤቱ ያሉ ተማሪዎችም ሆነ መምህራን የትምህርት ቤቱ ወሳኝ ኣካላት ናቸው። ኣለቃና ምንዝር የሚል መዋቅር የለውም።

በትምህርት ቤቱ የሚሰሩ ስራዎች ሁሉም በበጎ ፍቃድ የሚከናውን ሲሆን ለሚሰጥው ኣገልግሎት ክፍያ ኣይደረግም። ሆኖም ኣንዳንድ ስራዎችን ቀጣይነት ለማስተባበር ኣንድ ተቀጣሪ ሰራተኛ ኣለው።

እያንዳንዱ የስራ ቡድኖች የየራሳቸውን ሃላፊነት ያለተጽእኖ የሚያከናዉኑ ሲሆን የትምህርት ቤቱን ሂደት በሚመለከት የሚደረጉ ዉሳኔዎች በወር ኣንድ ጊዜ በሚደረግ ኣጠቃላይ ስብሰባ ውሳኔ መሰረት ይሆናል።

ማንኛውን የትምህርት ቤቱ ኣባል ሃሳቡን ኣቅርቦ ስምምነት ሲደረስ ወደ ተግባር የሚተረጉምበት መድረክ ክፍት ነው።

በመሆኑም ሁሉም ተሳትፎ ለማድረግ የሚችሉበት መድረክ ክፍት ነው።

ኣድራሻ

Sihlquai 125, 8005 Zürich

info@bildung-fuer-alle.ch

የትምህርት ሰኣት